በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ የኮሌራ ወረርሽ በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ ነው


ፋይል - በማላዊ ብላንቲር ከተማ በሚገኘው ሊምቤ ክሊኒክ በኮሌራ በሽታ የተጠቃ ታካሚ በጤና ሰራተኛ ርዳታ ሲያገኝ
ፋይል - በማላዊ ብላንቲር ከተማ በሚገኘው ሊምቤ ክሊኒክ በኮሌራ በሽታ የተጠቃ ታካሚ በጤና ሰራተኛ ርዳታ ሲያገኝ

በምሥራቅ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመንግስት ወታደሮችና በአማጺያን መካከል እየተካሄደ ያለው ውጊያ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩትን በማፈናቀሉ፣ የኮሌራ ወረርሽኝ በአሳሳቢ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ መሆኑንና “የጤና ቀውስ” ሊከተል እንደሚችል ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን አስጠንቅቋል።

የሐኪሞች ቡድኑ ባለፉት አሥር ቀናት ውስጥ በጎማ ከተማ አቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ 7 ሺህ 256 በኮሌራ የተያዙ ሰዎች መምጣታቸውን አስታውቋል። ከነዚህ ውስጥ ሶስት እጅ የሚሆኑት ከ 5 ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ ሕጻናት እንደሆኑ የረድኤት ድርጅቱ አስታውቋል።

ኤም-23 የተባለው አማጺ ቡድን ጥቃት ሲሰነዝር የሸሹ ከ177 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ኒራጎንጎ በተባለ ስፍራ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ የገኛሉ ሲል የሐኪሞች ቡድኑ በመግለጫው ጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG