በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሌራ ወረርሽኝ በሄይቲ እየተዛመተ ነው


ፋይል - አንድ በኮሌራ በሽታ የተያዘ ወጣት በሄይቲ፣ ፖርት ኦ ፕሪንስ የሚገኘው እና በድምበር የለሽ ዶክተሮች ተቋም የሚንቀሳቀሰው ክሊንክ ለህክምና ሲደርስ
ፋይል - አንድ በኮሌራ በሽታ የተያዘ ወጣት በሄይቲ፣ ፖርት ኦ ፕሪንስ የሚገኘው እና በድምበር የለሽ ዶክተሮች ተቋም የሚንቀሳቀሰው ክሊንክ ለህክምና ሲደርስ

የኮሌራ ወረርሽኝ በሄይቲ እየተዛመተ ሲሆን የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከተጠየቀው 145 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የተገኘው 16 በመቶው ብቻ ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

ኮሌራ በሄይቲ እየጨመረ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን ወደ አካባቢው አገሮችም እየተዛመተ ነው ሲሉ በአገሪቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ኡልሪካ ሪቻርድሰን ኒው ዮርክ ላይ ዛሬ ተናግረዋል።


የመንግስታቱ ድርጅት ትናንት እንዳታወቀው በወረርሽኙ 283 ሰዎች ሲሞቱ 12 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ሆስፒታል ገብተዋል። 14 ሺህ በበሽታው የሚጠረጠሩ ሰዎችም ይገኛሉ ብሏል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ 155 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።

ወሮበሎች የመዲናዋን ፖርት ኦ ፕሪንስ 60 በመቶ መቆጣጠራቸው ችግሩን እንዳባባሰው ተጠቁሟል።

ዝቅተኛ የማኅበረሰብ ዕድገትና የሃብት ኢፍትሃዊነት ውጤት ተደርጎ የሚታየው ኮሌራ አሁንም የዓለም ህብረተሰብ ጤና ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG