በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሩሲያ ሲዋጋ የሞተው ዛምቢያዊ ተማሪ አስከሬን ወደ አገሩ ሊመለስ ነው


ፋይል - በደቡብ ሩሲያ ሮስቶቭ ኦን ዶን ቀጠና በሚሰጠው ወታደራዊ ስልጠና አዲስ ተመልማዮች በታንክ ላይ ቆሞ የሚያስረዳውን አሰልጣኝ ሲያዳምጡ
ፋይል - በደቡብ ሩሲያ ሮስቶቭ ኦን ዶን ቀጠና በሚሰጠው ወታደራዊ ስልጠና አዲስ ተመልማዮች በታንክ ላይ ቆሞ የሚያስረዳውን አሰልጣኝ ሲያዳምጡ

በሩሲያ እስር ውስጥ የነበረና በኋላም ዩክሬን ውስጥ ሲዋጋ ህይወቱ ያለፈው ተማሪ አስከሬን በመጪው እሁድ ወደ አገሩ ዛምቢያ እንደሚላክ የሀገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የ23 ዓመቱን ተማሪ ለመካኒ ናታን አሟሟት በተመለከተ ሉሳካ ሞስኮን አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቃ ነበር። ለመካኒ ከሩሲያ ወገን ሆኖ ሲዋጋ ባለፈው መስከረም መሞቱ ታውቋል።

በድኑ ዛሬ ዓርብ ሞስኮ እንደደረሰና፣ ከነገ በስቲያ ዛምቢያ እንደሚደርስ የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ስታንሊ ካኩቦ አስታውቀዋል።

የሩሲያ ቅጥር ወታደራዊ ሃይል የሆነው ‘ዋግነር ግሩፕ’ ሃላፊ ባለፈው ወር ሲናገሩ፣ መካኒ ከእስር ቤት መመልመሉን አምነው፣ ወደ ውጊያ የገባው ግን በፈቃደኝነት ነው ብለዋል።

ለወታደራዊ አገልግሎት ሲባል ሩሲያ ለእስረኞች ምዕረት እንደምታደርግ፣ እንዳለመታደል ሆኖ ግን መካኒ በጦር ሜዳ እንደትገደለ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጨምረው መናገራቸውን ኤ.ኤፍ.ፒ በዘገባው አመልክቷል።

ለቤተሠቡ የሚሰጠውን ካሳ በተመለከተ ወደፊት ውይይት እንደሚደረግበት ሚኒስትሩ አክለዋል።

መካኒ በሞስኮ የኑክሌር ኢንጂነሪንግ ትምህርቱን በመከታተል ላይ እንደነበረና፣ ከሁለት ዓመት በፊት ግን አደንዛዥ እጽ በመያዝ ተከሶ ዘጠኝ ዓመት ከስድስት ወር እስራት ተፈርዶበት ነበር።

XS
SM
MD
LG