በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ በ2023 እርዳታ ጠባቂ 26 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል - ተመድ


ኢትዮጵያ ውስጥ በ2023 እርዳታ ጠባቂ 26 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል - ተመድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:56 0:00

ኢትዮጵያ ውስጥ በ2023 እርዳታ ጠባቂ 26 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል - ተመድ

በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የሰሜን አካባቢዎች ወደ ሩብ ሚሊየን ኲንታል ምግብና መድሃኒት ማከፋፈሉን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሃት መካከል ደቡብ አፍሪካ ላይ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ሰብዓዊ ድጋፎችን ወደ ትግራይ፣ አማራና አፋር አካባቢዎች በመንገድ የማድረስ ሁኔታው መሻሻሉን ገልጿል።

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የአላማጣ ነዋሪ በዘላቂነት ሊቋቋሙ የሚችሉባቸው ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ጠይቀዋል።

በአንፃሩ አፋር ክልል ያሉ ሌላ አስተያየት ሰጭ በአካባቢው የሚገኙ የመሠረተ ልማት መዋቅሮች መውደማቸውን ተከትሎ እርዳታው በሚነገረው ልክ ባለመሆኑ ማኅበረሰቡ ችግር ላይ ነው ብለዋል።

ዓለምአቀፍ ለጋሾች በመጭው የአውሮፓ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር አሁን ካለበት ሃያ ሚሊየን ወደ 26 ሚሊየን ሊያድግ እንደሚችል ገምተው ያን ያህል ቁጥር ላለው ሰው ድጋፍ ለማድረስ 3.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም በዛሬ ምንዛሪ ወደ 190 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ቢሮው አሳስቧል።

XS
SM
MD
LG