በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞች ከመንገደኛ አውሮፕላን ወጥተው አመለጡ


ፍልሰተኞች ከመንገደኛ አውሮፕላን ወጥተው አመለጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:39 0:00

ፍልሰተኞች ከመንገደኛ አውሮፕላን ወጥተው አመለጡ

ከሞሮኮ ወደ ቱርክ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን ለድንገተኛ ጉዳይ ባርሴሎና ላይ ሲያርፍ፣ 28 የሚሆኑ ተጓዦች መንደርደሪያውን አስፋልት በሩጫ አቋርጠው መጥፋታቸውን የስፔን መንግስት አስታውቋል።

አውሮፕላኑ ኤል ፕራት በተሰኘው የባርሴሎና አየር ማረፊያ ለማረፍ የተገደደው አንዲት ነፍሰጡር መንገደኛ ድንገት ለመውለድ ተቃርባለች ሲባል ነበር።

አውሮፕላኑ እንዳርፈ ወዲያውኑ 28 የሚሆኑት ተሳፋሪዎች በሩጫ ለማምለጥ የሞከሩ ሲሆን ነፍሰ ጡሯን ጨምሮ አስራ ስድስቱን ፖሊስ ወዲያውኑ ይዟቸዋል፣ አስራ ሁለቱን ደግሞ ፍለጋ ላይ ነው።

ፖሊስ ከተያዙት አምስቱን በመጡብት የቱርክ አየር መንገድ የሚያስተዳድረው አውሮፕላን መልሶ አሳፍሯቸዋል። ቢያንስ ስምንት የሚሆኑት ደግሞ ወደ ሞሮኮ ተመልሰው ይላካሉ መባሉን የሮይተርስ ይዜና ወኪል ከሥፍራው ዘግቧል።

ልትወልድ ነበር የተባለችው ተጓዥ በሆስፒታል ምርመራ ተደርጎላት ምጥ ላይ እንዳልነበረች የስፔን መንግስት አስታውቋል። አውሮፕላኑ 228 ተጓዦችን ይዞ ከካዛብላንካ ወደ ኢስታንቡል በማቅናት ላይ ነበር።

ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በሃሰት ድንገተኛ በተባለ ጉዳይ አንድ መንገደኞችን የያዘ አውሮፕላን ስፔን ውስጥ ማሎርካ በተባለች ደሴት ሲያርፍ በርካታ መንገደኞች አምልጠዋል። አስራ ሁለቱ ሲያዙ፣ ሌሎች አስራ ሁለት የሚሆኑት ደግሞ ሳይገኙ ቀርተዋል።

XS
SM
MD
LG