በትግራይ ክልል በአክሱምና ዓድዋ ከተሞች በጥቂት ቀናት ውስጥ የስልክ አገልግሎት እንደሚጀመር ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡ ባለፈው ሳምንት በሙከራ ላይ የነበረው የሽረ ከተማ የስልክ ግንኙነትም በይፋ መጀመሩን የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሳይ ውብሸት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሽረ ከተማ ነዋሪዎች የስልክ አገልግሎቱ በዚህ ሳምንት መጀመሩን ገልፀው፣ የጥራት ችግር እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ በሽረ ከተማ የስልክ አገልግሎቱ በዚህ ሳምንት መጀመሩን ቪኦኤ ከስፍራው ማረጋገጥ ችሏል፡፡
አንዲት የከተማዋ ነዋሪ መስመሩ የጥራት ችግር ቢኖርበትም ጓደኞቿን በማግኘቷ መደሰቷን ገልፃለች። ቴዎድሮስ ኃይለ የተባለ የአክሱም ተወላጅ ለሙከራ በተለቀቀው የስልክ አገልግሎት የአባቱን ድምፅ መስማቱን ገልጾልናል። /ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/