በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኪረሙና አንገር ጉቴ ወረዳዎች ውስጥ በተፈፀሙ ጥቃቶች ብዙ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ


ኪረሙና አንገር ጉቴ ወረዳዎች ውስጥ በተፈፀሙ ጥቃቶች ብዙ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:37 0:00

ኪረሙና አንገር ጉቴ ወረዳዎች ውስጥ በተፈፀሙ ጥቃቶች ብዙ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ እና አንገር ጉቴ ወረዳዎች ውስጥ ከኅዳር 9 ጀምሮ እየተፈጸሙ ነው በተባሉ ጥቃቶች ቁጥሩ የበዛ ሰው መገደሉንና በሺሆች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በህይወትና በአካል ላይ ስለደረሰው ጉዳት መጠን የተረጋገጡ ቁጥሮችን ማግኘት አልቻልንም።

የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑ አስተያየት ሰጪዎች ለጥቃቶቹ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልንና ኦነግ ሸኔ ያሉትን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ ሲያደርጉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በበኩላቸው ጽንፈኛና ፋኖ የሚሏቸውን ታጣቂዎች እየወነጀሉ ነው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዞኑ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበውና መረጃ በማሰባሰብ ላይ መሆኑን ለቪኦኤ ገልጿል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግሥት ጥቃቶቹን እንዲያስቆምና የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት እንዲጠብቅ እየጠየቁ ነው፡፡

ከፌደራል መንግሥቱ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። የአሜሪካ ድምፅም በርካታ ሙከራዎችን አድርጎ አልተሳካም።

XS
SM
MD
LG