በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጀርመን መፈንቅለ-መንግስት ሊያደርጉ አቅደው ነበር የተባሉ ተያዙ


 የጀርመን አክራሪ ቡድን አባላት
የጀርመን አክራሪ ቡድን አባላት

በሺህ የሚቆጠሩ ፖሊሶች በመላ ጀርመን አሰሳ አድርገው በትጥቅ ሃይል መፈንቅለ-መንግስት ሊያደርጉ አቅደው ነበር ያሏቸውን 25 ቀኝ አክራሪዎችን ይዘው አስረዋል።

አቃቤ-ሕግ እንዳለው 3 ሺህ የሚሆኑ ፖሊሶች በ11 ግዛቶች ባደረጉት አሰሳ “ራይኽ ስትዝን” የተሰኘው የአክራሪዎች እንቅስቃሴ አባላትን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

የንቅናቄው አባላት ጀርመን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የምትመራበትን ሕገ-መንግስት በማጣጣል መንግስትን ለመገርሰስ ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል ተብሏል።


የጀርመኑ የፍትህ ሚኒስትር ማርኮ በሽማን ዘመቻውን “የፀረ-ሽብር ዘመቻ” ሲሉ ገልጸውታል። ተጠርጣሪዎች በመንግስት ተቋማት ላይ ጥቃት ሳያቅዱ አልቀሩም ሲሉም አክለዋል።


ንቅናቄው ደም አፋሳሽ የመንፈንቅለ-መንግስት ሃሳቦች የሚያማልለውና በሤራ ወሬዎች የተጠመደ ነው ሲሉ የጀርመን ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች ይናገራሉ።


አቃቤ-ሕግ እንደሚለው 22 የጀርመን ዜጎች በሽብር ድርጅት ዓባልነት ተጠርጥረው ሲያዙ፣ የሩሲያ ዜግነት ያለውን ግለሰብ ጨምሮ ሶስት ሌሎች ደግሞ የሽብር ድርጅትን በመደገፍ ተጠርጥረው ታስረዋል። ሌሎች 27 ሰዎች ደግሞ በምርመራ ላይ እንደሆኑ የአሶስዬትድ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG