በኒው ዮርክ የሚገኝ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ድርጅት በታክስ ማጭበርበር በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ነው ሲል ትንንት በይኗል።
ጥፋተኛ የተባሉትም የድርጅቱ ከፍተኛ ሃላፊዎች ለአፓርትመንት እና ቅንጡ መኪና ለመሰሉ ጥቅማ ጥቅሞች የገቢ ግብር ባለመክፈላቸው መሆኑ ተገልጿል። ምርመራው ለሶስት ዓመታት ሲከናወን ነበር።
ድርጅቱ 1.6 ሚሊዮን ዶላር መቀጫ እንደሚጠብቀው ታውቋል።
የትረምፕ ድርጅቶች የረጅም ግዜ የገንዘብ ሃላፊ የነበሩት አለን ዋይስልበርግ ለ15 ዓመታት የተካሄደውን የታክስ ማጭበርበር በተመለከተ ጥፋተኝነታቸውን አምነዋል። በፍርድ ሂደቱ ወቅት ምስክርነታቸውን የሰጡት የ5 ወራት እስር ብቻ ቃል ተገብቶላቸው ነው ተብሏል።
የትረምፕ ድርጅቶች የተለያዩ የታክስ ማጭበርበር ክሶች ቢኖርባቸውም፣ የትናንቱ የጥፋተኝነት ውሣኔ የመጀመሪያው እንደሆነ ታውቋል።