በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጆርጂያ ዲሞክራቶች አሸንፈው ሴኔቱን ተቆጣጠሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዝዳንት አማካይ የስልጣን ዘመን የማጠናከሪያ ምርጫ በጆርጂያ
የዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዝዳንት አማካይ የስልጣን ዘመን የማጠናከሪያ ምርጫ በጆርጂያ

በዩናይትድ ስቴትስ ለሕግ መወሰኛ ም/ቤት መቀመጫ ትናንት ማክሰኞ በጆርጂያ በተካሄደው የማጠናከሪያ ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ወኪሉ ራፋኤል ዋርኖክ በድጋሚ ተመርጠው አሸንፈዋል።

በዚህም የዲሞክራቲክ ፓርቲው የሕግ መወሰኛ ም/ቤቱን 51 ለ 49 በሆነ የመቀመጫ ልዩነት መቆጣጠር ችሏል። ባለፈው ወር በተደረገው የተወካዮች ም/ቤት ምርጫ ሪፐብሊካን ፓርቲው መቆጣጠሩን አረጋግጧል። በመሆኑም ለሁለት የተከፈለ መንግስት ይሆናል ተብሏል።

ራፋኤል ዋርኖክን ባለፈው የምርጫ ዘመን ግዛቲቱን በሴናተርነት ወክለዋል።

በዋርኖክና በሪፑብሊካን ወኪሉ ኽርሸል ዎከርን መካከል የተደረገው ምርጫ ከፍተኛ ፉክክር የታየበትና፣ ከዚህ በፊት ያልታየ የመራጮች ቁጥር መጠን የተመዘገበበት ነው ተብሏል።

በጆርጂያ የሪፐብሊካን ፓርቲው ሽንፈት፣ በቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ አምሳያ የቀረቡት እጩዎች በየግዛቱ የገጠማቸውን ፈተና የሚያሳይና፣ ትረምፕ ለሶስተኛ ግዜ ለምርጫ ለመወዳደር የሚያደርጉት ጥረት ላይ ውሃ የቸለሰ ነው ተብሏል።

XS
SM
MD
LG