በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ከባንክ የሚወጣ ገንዘብ መጠንን ወሰነች


ፋይል - የናይጄሪያ የገንዘብ ኖት የሆነው ናይራ
ፋይል - የናይጄሪያ የገንዘብ ኖት የሆነው ናይራ

አስመስሎ የሚሠራ ገንዘብንና፣ ከጠለፋ በኋላ የሚጠየቀውን የቤዛ ክፍያ ለማስቆም ነው በሚል ናይጄሪያ በየሳምንቱ ከባንክ በሚወጣ ጥሬ ገንዘብላ ላይ የመጠን እገዳ ጥላለች።

የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ትናንት እንዳስታወቀው ግለሰቦች በሳምንት ከባንክ ማውጣት የሚችሉት ገንዘብ መጠን 100ሺህ ናያራ ወይም 225 ዶላር ብቻ ነው።

ከአዲሱ ደንብ በፊት በቀን እስከ 1.5 ሚሊዮን ናያራ ወይንም 3ሺህ 375 ዶላር ነበር።

የንግድ ድርጅቶች በአዲሱ ደንብ መሠረት በሳምንት 500 ሺህ ናያራ ማውጣት ይችላሉ። ከዚህ በፊት በቀን እስከ 3 ሚሊዮን ማውጣት ይችሉ ነበር።


ከባንክ ሥርዓት ውጪ ያለው የገንዘብ መጠን አሳሳቢ እንደሆነና ገንዘብ አስመስሎ ማተም እየተባባሰ እንደሆነ እንዲሁም ለጠላፊኦች የሚከፈለው የገንዘብ መጠን አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ማዕከላዊ ባንኩ ከዚህ ቀደም ሲገልጽ ቆይቷል።


አዲሱ የማዕከላዊ ባንክ ፖሊሲ በሚቀጥለው የካቲት በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፖለቲከኞች ድምጽን በገንዘብ ከመግዛትና ምርጫውን በገንዘብ ሃይል ከማከናወን እንዲታቀቡ ለማድረግ የወጣ ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች በበኩላቸው ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG