በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓርላማ አባሏ በጥፊ መመታት በሴኔጋል እያነጋገረ ነው


አንዲት ሴት የፓርላማ አባል በሌላ ወንድ አባል በምክር ቤት ውስት በጥፊ ሲመቱ
አንዲት ሴት የፓርላማ አባል በሌላ ወንድ አባል በምክር ቤት ውስት በጥፊ ሲመቱ

በአፍሪካ ጠንካራ ዲሞክራሲ ካሏቸው አገራት አንዱ ተደርጋ የምትታየው ሴኒጋል፣ በአገሪቱ አንድ ሴት የፓርላማ አባል በሌላ ወንድ አባል በምክር ቤት ውስት በጥፊ ከተመቱ በኋላ ፣ የዲሞክራሲ ባህላቸው ላይ ጠንካራ ጥያቄ ተነስቷል።

ባለፈው ሐሙስ የተፈጠረው ክስተት በሶስት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑ ነው።

በፍትሕ ሚኒስቴር በጀት ላይ ላይ ክርክር በሚደረግበት ወቅት፣ ተቃዋሚ የፓርላማ ዓባል ማሳታ ሳምብ የመንግስት ተወካዩዋን ኤሚ ዳዬን በጥፊ ብለዋቸዋል።

ግለሰቧ በአጸፋው ወንበር አንስተው ቢወረውሩም፣ ሌላ የፓርላማ አባል ሆዳቸውን በእርግጫ ብሉ ጥሏቸዋል። ከዛም ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

ጠበቃቸው እንደሚሉት ኤሚ ነፍሰ ጡር ናቸው። ጽንሱን ሊያጡ ይችላሉ የሚልም ፍርሃት አለ።

ድርጊቱ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን በተመለከተ አገር አቀፍ ዘመቻ በሚደረግበት ወቅት የተፈጸመ በመሆኑ፣ ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሏል ሲል ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG