በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔት ድጋሚ ምርጫ በጆርጂያ


ለጆርጂያ ግዛት የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የሚወዳደሩት የሪፐብሊካን ወኪል የሆኑት ኸርሼል ዎከር በስተግራ እና የዲሞክራቲክ እጩ የሆኑት ራፋኤል ዋርኖክ በቀኝ
ለጆርጂያ ግዛት የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የሚወዳደሩት የሪፐብሊካን ወኪል የሆኑት ኸርሼል ዎከር በስተግራ እና የዲሞክራቲክ እጩ የሆኑት ራፋኤል ዋርኖክ በቀኝ

በዩናይትድ ስቴትስ ለሕግ መወሰኛ ም/ቤት መቀመጫ ድጋሚ ምርጫ የሚካሄድባት የጆርጂያ ግዛት ነዋሪዎቿ ድምጽ በመስጠት ላይ ናቸው። ባለፈው ወር በተደረገው ምርጫ አሸናፊው ሳይለይ ቀርቷል።


የጆርጂያ ነዋሪዎች የዲሞክራቲክ ፓርቲ ወኪል የሆኑትን ራፋኤል ዋርኖክን ደግሞ በመመምረጥ ወይንም የቀድሞ ስፖርተኛ የነበሩትን የሪፐብሊካን ወኪል ኽርሸል ዎከርን አዲስ ወኪል ማድረግ በሚለው ላይ ውሳኔ ይሰጣሉ።

ባለፈው ምርጫ ዋርኖክ በ 37 ሺህ ድምጽ ቢመሩም ለማሸነፍ ያሚያስፈልጋቸውን የድምጽ መጠን ሳያገኙ ቀርተዋል። በተደረገው የምረጡኝ ዘመቻ ከፍተኛ ገንዘብ መውጣቱ የተገለጸ ሲሆን ዋርኖክ 150 ሚሊዮን ዶላር ሲያወጡ፣ ሪፐብሊካኑ ዎከር ደግሞ 60 ሚሊዩን ዶላር አፍስሰዋል ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።


ሁለቱም ተፎካካሪዎች ጥቁር አሜሪካውያን ሲሆኑ፣ ሪፐብሊካኑ ዎከር የአሜሪካ እግር ኳስ በመጫወት መታወቃቸውን ተጠቅመው ለውድድር ቀርበዋል። በተጨማሪምዎከር ለሁለት የቀድሞ ሴት ጓደኞቻቸው ጽንስ ለማቋረጥ ገንዘብ ሰጥተዋል የሚል ክስም ይቀብባቸዋል። ዎከር በበኩላቸው ዋርኖክን ለፕሬዝደንት ባይደን ፍጹም ታዛዥ ናቸው ሲሉ ይነቅፏቸዋል።

በዚህ ምርጫ ዲሞክራቶች ካሸነፉ የህግ መወሰኛ ም/ቤቱን 51 ለ 49 ይመሩታል ማለት ነው። ካልሆነ ግን 50 እኩል መቀመጫ ይኖራቸውና፣ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት ዲሞክራቲኳ ካመላ ሃሪስ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ፕሬዝደንትም በመሆናቸው ባላቸው አንድ ገላግሌ ድምጽ ም/ቤቱን ይቆጣጠሩታል።

XS
SM
MD
LG