በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኮንጎን ችግር እያባባሰው ነው ስትል ሩዋንዳ ከሰሰች


ፋይል - የኤም 23 ተዋጊዎች በዲሞክራቲክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኘው ሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ጎማ 62 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ካሩባ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ይታያል።
ፋይል - የኤም 23 ተዋጊዎች በዲሞክራቲክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኘው ሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ ጎማ 62 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ካሩባ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ይታያል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሩዋንዳ የኤም-23 አማጽያንን መርዳቷን እንድታቆም መጠየቋን ተከትሎ፣ የሩዋንዳው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኮንጎ ያለውን ቀውስ እያባባሰው ነው ሲሉ ከሰዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ባለፈው እሁድ የሩዋንዳውን ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜን በስልክ አግኝተው በኮንጎ ላሉ አማጽያን የሚደርገ የውጪ እገዛ መቆም እንዳለበትና ይህም ሩዋንዳ ለኤም-23 የምትሰጠውን እንደሚጨምር ነግረዋቸው ነበር።

ሩዋንዳ ለኤም-23 ድጋፍ ትሰጪያለሽ የሚለውን የአሜሪካ ክስ ደጋግማ አስተባብላለች። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለልተኛ ባለሙያዎችም ኪጋሊ ለኤም-23 ድጋፍ እንደምትሰጥ መረጃ እንዳላቸው ሲገልጹ ቆይተዋል።


የሩዋንዳው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰንት ብሩታ ካጋሜ እና ብሊንከን “መልካም ውይይት አድርገዋል፣ ችግሮችን በመረዳት ረገድ ግን ልዩነቶች እንዳሉ ነው” ማለታቸውን የ ኤ.ኤፍ.ፒ. ዜና ወኪል ዘግቧል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተንጋደደ አረዳድ በኮንጎ ያለውን ችግር እያባባሰው ነው ሲሉም አክለዋል።

ባለፈው ሳምንት በኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል 300 የሚሆኑ ሲቪሎች በኤም-23 ተገድለዋል ስትል ኪንሻሳ ከሳለች።

XS
SM
MD
LG