በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤ.ኤን.ሲ በራማፎሳ ላይ የቀረበውን ውንጀላ ውድቅ አደረገ


የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ብሄራዊ ማዕከላዊ ኮሚቴ በጆሃንስበርግ ባካሄደው ስብሰባ ለመካፈል ሲደርሱ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ብሄራዊ ማዕከላዊ ኮሚቴ በጆሃንስበርግ ባካሄደው ስብሰባ ለመካፈል ሲደርሱ

የደቡብ አፍሪካው ገዢ ፓርቲ ኤ.ኤን.ሲ በፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ላይ የቀረበውንና ከገጠር ቤታቸው ተሠረቀ የተባለውን ገንዘብ የተመለከተውን ክስ በፓርላማ መቀመጫ የያዙ አባላቱ ውድቅ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

ኤ.ኤን.ሲ አቋሙን እንዳስታወቀ ወዲያውኑ፣ ራማፎሳም የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱን ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በፓርላማ የተቋቋመ ገለልተኛ መርማሪ ቡድን ከራማፎሳ የገጠር መዝናኛ ቤት ተሠረቀ የተባለው ግማሽ ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በታክስ ሪፖርት ላይ ያልታየና ምንጩ የማይታወቅ ነው በማለት፣ ራማፎሳ የእምነት ማጉደል ሳይፈስሙ አይቀርም፣ ሥልጣን ሲረከብቡ የገቡትን ቃለ መሃላም አልጠበቁም ሲል ቀርበው መልስ እንዲሰጡ ባለፈው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት ጠይቆ ነበር።

“ፕሬዝደንቱ ሪፖርቱን በደንብ ተመልክተውታል። ነገ ፓርላማው ተሰብስቦ ለማጽደቅ የሚሞክር ከሆነ፣ በፓርላማው የሚገኙት የኤ.ኤን.ሲ አባላት የተቃውሞ ድምጽ ይሰጣሉ።” ብለዋል ፖል ማሻታይል የገዢው ኤ.ኤን.ሲ ፓርቲ ዋና ገንዘብ ያዥ።

የራማፎሳ ተቃዋሚዎች ግን “ፋርምጌት” ብለው በሚጠሩት ክስ ምክንያት ስልጣን መልቀቅ አለባቸው የሚል ግፊት እያደረጉ ነው።

በፓርላማው አፈ-ጉባኤ የተቋቋመው አጣሪ ቡድን ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ በራማፎሳ የገጠር ቤት ሶፋ ሥር ከተደበቀበት መሠረቁን ነገር ግን ፕሬዝደንቱ ክስተቱን ሪፖርት ሳያደርጉ ማለፋቸውን ባለፈው ሳምንት አስታውቋል።

የገንዘቡ በቤታቸው ተገኘ መባል ሌብነትን ለመዋጋት ቃል ገብተው ስልጣን በያዙት ራማፎሳ ላይ ጥርጣሬ አስከትሏል።

ራማፎሳ ውንጀላውን ያስተባበሉ ሲሆን እስከ አሁንም በወንጀል የጠየቃቸው የለም። የተሰረቀው ገንዘብም 20 ጎሾችን ለአንድ ሱዳናዊ ሸጠው ያገኙት እንደሁነ ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG