በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መምሕራን የሥራ ማቆም አድማ


የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መምሕራን የሥራ ማቆም አድማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00

የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መምሕራን የሥራ ማቆም አድማ

በተለያዩ ከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ውስጥ የሚያስተምሩ መምሕራን የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ። ከዚህ ቀደም ያነሷቸው የደሞዝ ጭማሪና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ምላሽ ባለማግኘቱ ምክኒያት አድማውን ማድረጋቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። መምሕራኑ የሚከፈላቸው ደሞዝ ከኑሮ ውድነቱ ጋር እንደማይጣጣም ገልፀው ኑሯቸውን ለመምራትም ሆነ የተመደቡበትን ሥራ ለመሥራት መቸገራቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምሕራን ማኅበር ግን በማኅበሩ ስም የተጠራ የሥራ ማቆም አድማ እንደሌለ ገልጿል፡፡

ማኅበሩ የመምህራኑን ጥቅማ ጥቅም ጨምሮ ሌሎች ጥያቄዎችን ለመንግሥት እንዳቀረበና ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑን ጠቁሞ “አብዛኛው ዩኒቨርሲቲዎች በሥራ ላይ ይገኛሉ” ብሏል፡፡

/ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG