በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃይማኖተኞችና የተመሳሳይ ጾታ መብት አቀንቃኞች ሙግት በጠቅላይ ፍ/ቤት


ፋይል - የድህረገፅ ንድፍ አውጪ ሎሪ ስሚዝ ኮሎራዶ በሚገኘው ሊትልታውን ከተማ በስራ ቦታዋ ላይ ሆና
ፋይል - የድህረገፅ ንድፍ አውጪ ሎሪ ስሚዝ ኮሎራዶ በሚገኘው ሊትልታውን ከተማ በስራ ቦታዋ ላይ ሆና

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ የክርስቲያን ሃይማኖት ተከታይ የሆነ የድህረ-ገጽ ንድፍ አውጪ፣ የተመሳሳይ ጾታ ጥንዶችን ሠርግ ድህረ ገጽ አልነድፍም የማለቱን ጉዳይ ዛሬ ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።


በአሜሪካ በሃይማኖተኞችና በተመሳሳይ ጾታ ነጻነት አቀንቃኞች መካከል የሚደረግ ሌላው ፍልሚያ ተደርጎም በመታየት ላይ ነው።


የኮሎራዶ ነዋሪ የሆነችው የድህረ-ገጽ ንድፍ አውጪ ሎሪ ስሚዝ እና አጋሮቿ ፍ/ቤቱ በእነርሱ ላይ የሚፈርድ ከሆነ፣ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ሰዓሊዎች፣ ፀሃፍት እና ሙዚቀኞች ሃይማኖታቸው የማይፈቅድላቸውን ነገር እንዲፈጽሙ ያስገድዳቸዋል ሲሉ ይከራከራሉ።


እንደ አሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ፣ የሎሪ ስሚዝ ተቀናቃኞች መከራከሪያ ደግሞ ፍርዱ ለእርሷ ካደላ አገልግሎት ሰጮዎች በጥቁሮች፣ አይሁዶች፣ ሙስሊሞች ስደተኞች፣ ቅይጥ ዘር ባላቸውና በሌሎችም ላይ አድልዎ እንዲፈጽሙ ያደርጋል የሚል ነው።


ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዘጠኙ ዳኞች ውስጥ ስድስቱ ወግ አጥባቂ ሲሆኑ፣ ከዚህ በፊት በወሰኗቸው ጉዳዮች ውስጥ ወደ ሃይማኖተኞች እንደሚያጋድሉ ታውቋል።


ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ የመጣው፣ ከጠቅላይ ፍ/ቤቱ ባሻገር የሚገኘው የአሜሪካ ኮንግረስ የተመሳሳይ ጾታ የትዳር መብትን የሚፈቅድ ረቂቅ ድንብ በማጠናቀቅ ላይ ባለበት ወቅት ነው።

XS
SM
MD
LG