በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ የባቡር አገልግሎት ጥቃት ከተፈጸመበት ስምንት ወራት በኋላ ስራ ጀመረ


በናይጄሪያ ካዱና ከተማ በሚያልፈው የባቡር ሃዲድ ዙሪያ ሰዎች ሲገበያዩ
በናይጄሪያ ካዱና ከተማ በሚያልፈው የባቡር ሃዲድ ዙሪያ ሰዎች ሲገበያዩ

ባለፈው መጋቢት ታጣቂዎች የባቡር ሃዲድና ተጓዥ ባቡርን በከፍተኛ ፍንዳታ አውድመው፣ ተኩስ በመክፈት 8 ገድለው 26 ካቆሰሉ በኋላ ተዘግቶ የነበረውና የናይጄሪያን መዲና ከሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ጋር የሚያገናኘው የባቡር መንገድ ዛሬ ሰኞ እንደገና መከፈቱን የኤ.ኤፍ.ፒ ሪፖርት አመልክቷል።


በአገሪቱ ከተፈጸሙት ከፍተኛ ጥቃቶች አንዱ ነው በተባለው ያለፈው መጋቢት ጥቃት ከውድመትና ከሰው ሞት በተጨማሪ አጥቂዎቹ በርካታ ተጓዦችን አግተው የነበር ሲሆን ከአጋቾቹ ጋር በተደረገ ድርድር ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ ታጋቾች ቀስ በቀስ መለቀቃቸው ይታወሳል። አጋቾቹ ጠቀም ያለ ቤዛ እንደተቀበሉም ታውቋል።


አቡጃን ካዱና ከተባለች የአገሪቱ ሰሜናዊ ከተማ የሚያገናኘው ባቡር ዛሬ ጠዋት መነሳቱን፣ ነገር ግን አንድ ሶስተኛ ተሳፋሪዎችን ብቻ እንደያዘ የተገለጸ ሲሆን መስመሩ በመከፈቱ ግን ተገልጋዮች ደስተኛ መሆናቸውን በባቡር ጣቢያው ከተገኘው የኤ.ኤፍ.ፒ ዘጋቢ ለማወቅ ተችሏል።

ነገር ግን አሁንም የደህንነታቸው ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ተሳፋሪዎቹ አልሸሸጉም።

XS
SM
MD
LG