በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን አዲስ በሲቪል የሚመራ የሽግግር መንግስት ለመመሥረት ስምምነት ተደረገ


ፋይል - ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደ ከአንድ አመት በኃላ፣ የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች የሲቪል አገዛዝ እንዲመለስ በካርቱም ሱዳን ያካሄዱት ሰልፍ
ፋይል - ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደ ከአንድ አመት በኃላ፣ የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች የሲቪል አገዛዝ እንዲመለስ በካርቱም ሱዳን ያካሄዱት ሰልፍ

የሱዳን ጄኔራሎች እና የዲሞክራሲ አቀንቃኝ ቡድን በአገሪቱ አዲስ በሲቪል የሚመራ የሽግግር መንግስት ለመመሥረት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።


በስምምነቱ መሠረት በሲቪል የሚመራው የሽግግር መንግስት አገሪቱን ለምርጫ በማዘጋጀት ወደፊት የምትመራበትን መንገድ ያመቻቻል።


ስምምነቱ የተፈረመው በሁለት የሱዳን ከፍተኛ ጄኔራሎች፣ ማለትም ጄኔራል አብደል-ፈታ አል-ቡርሃን እና ጄኔራል ሃምዳን ዳጋሎ በአንድ ወገን አንዲሁም የነጻነትና የለውጥ ሃይሎች የተሰኘውና በአገሪቱ የሚገኘው ትልቁ የዲሞክራሲ አቀንቃኝ ቡድን መሪዎች በሌላ ወገን እንደሆነ የአሶስዬትድ ፕሬስ ሪፖርት አመልክቷል።


ነገር ግን በርካታ የሱዳን ተቃዋሚ ቡድኖች ከስምምነቱ ውጪ ለመሆን ወስነዋል። ከነዚህ አንዱ ሰፊ መሠረት ያለውና ‘ሬዚስታንስ ግሩፕ’ የተሰኘው ቡድን አገሪቱን እየመሩ ካሉት ጄኔራሎች ጋር እንደማይነጋገር ሲያስታወቅ ከርሟል።


ስምምነቱ የሱዳን ሰራዊት ከፖለቲካ ገለል እንደሚል፣ በተጨማሪም ‘አብዮታዊ ሃይሎች’ ብለው የሚጠሯቸውና ስምምነቱን የፈረሙ ቡድኖች አገሪቱን ለሁለት የሽግግር ዓመታት የሚመራ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚመርጡ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG