በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያዊያን ለዩክሬኑ ጦርነት ይሰጡ የነበረው ህዝባዊ ድጋፍ ቀንሷል ሲል የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ


የሩሲያ ወታደር
የሩሲያ ወታደር

የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስቴር በቅርቡ በተካሄደ የህዝብ አስተያየት ስብሰባ ሩሲያ በዩክሬን ለምታካሂደው ጦርነት ህዝባዊ ድጋፏ እየወደቀ ነው ብለዋል።

የብሪታኒያ ደህንነት እሁድ ጠዋት ባደረገው መግለጫ ከሩሲያ ገለልተኛ መገናኛ ብዙሃን አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት 55 ከመቶ የሚሆኑ ሩሲያዊያን የሰላም ድርድር እንደሚመርጡ ያስታወቀ ሲሆን 25 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ጦርነቱ እንዲቀጥል እንደሚደግፉ ገልጿል።

ባለፈው ዓመት በጎርጎሮሳዊያኑ ሚያዚያ 2022 80 ከመቶ የሚሆኑ ሩሲያዊያን ጦርነቱን ይደግፉ እንደነበር ሪፖርቱ አክሎ ጠቁሟል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “በሚቀጥሉት በርካታ ወራት ሩስያ ትልቅ የጦር ሜዳ ስኬቶችን ስለማታገኝ ክሬምሊን የህዝብ ድጋፍ እንዳገኘ መቆየት ይከብደዋል” ሲል አስታውቋል።

በሌላ በኩል የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ የሩሲያ የባህር ወለድ ዘይት በበርሜል 60 ዶላር ዋጋ እየተሸጠ መሆኑ የሩሲያን ምጣኔ ሃብት ላይ ጫና ለማሳደር በቂ አይደለም ብለዋል።

ይህ የዋጋ ጣሪያ አውስትሬሊያ፣ ብሪታኒያ፣ ካናዳ፣ ጃፓን፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት መሃከል በተደረሰ ስምምነት የወጣ ቢሆንም ዘለንስኪ ግን ቅዳሜ ዕለት ዋጋው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG