በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሽረው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ


የሽረው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:15 0:00

የሽረው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ

የሽረው የባለሞያዎች የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ የሠላም ሥምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ በሁለቱ አካላት መካከል ትልቅ መተማመንን የሚያጎለብት ነው ሲል የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ።

ኅብረቱ፣ የሥምምነቱ ትግበራ ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው መግለጫ፣ የአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ለሠላሙ ሂደት ትልቅ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም ገልጿል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ የጋራ ኮሚቴው ስብሰባ መጀመሩ በተነገረበት በትናንትናው ዕለት “የትግራይ ተዋጊዎች በሥራቸው ከነበሩ የውግያ ግምባሮች ለቀው መውጣት መጀመራቸውን” የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሥምምነቱ ተፈጻሚነት በቁርጠኝነት መሥራቱን እንደሚቀጥል በድጋሚ አስታውቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ “ለሠላም ሥምምንነቱ ትግበራ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ድጋፍ እየጨመረ እንደሚገኝ” ተናግረዋል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG