በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን ሃይማኖታዊ ት/ቤት ውስጥ በፈነዳ ቦምብ 15 ተማሪዎች ሞቱ


የአፍጋኒስታን ካርታ
የአፍጋኒስታን ካርታ

አፍጋኒስታን ውስጥ በሰሜን ሳማንጋን በሚገኝ ሀይማኖታዊ ትምህርት ቤት ውስጥ ዛሬ በደረሰ ፍንዳታ 15 ተማሪዎች ሲሞቱ 27 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን የአፍጋኒስታን ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

ፍንዳታው መድረሱን ለቪኦኤ በስክል ያረጋገጡት የማስታወቂያና ባህል ዳይሬክቶሬት ኢምዳዱላህ ማኻጀር የፍንዳታውን ዝርዝር አልገለጡም፡፡

ከካቡል የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አብዱ ናፊ ታኩር፣ አይባክ በተባለ የክፍለ ግዛቲቱ ከተማ የቦምብ ፍንዳታው የደረሰው ተማሪዎቹ የከሰዓት በኋላ ጸሎታቸውን በማድረስ ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጸጥታ ኃይሎች በሥፍራው ደርሰው ሁኔታውን እያጣሩ እንደነበርም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ለፍንዳታው እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ የለም፡፡

ዩናይትድ ስቴስቴት እና ምዕራባውያን አጋሮችዋ ከታሊባን ጋር ካደረጉት 20 ዓመታት ጦርነት በኋላ አፍጋኒስታንን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ታሊባን ሥልጣን ከያዘበት እአአ ከነሀሴ 2021 ጀምሮ አይሲስኬ የተባለው እስላማዊ ድርጅት ጥቃት መሰንዘር መጀመሩ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG