በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሐዋዩ ማኡና ሎአ እሳተ ጎመራ መፈንዳት ጀመረ


ፎቶ ፋይል፦ የሐዋዩ ማኡና ሎአ እሳተገሞራ እአአ 10/27/2022
ፎቶ ፋይል፦ የሐዋዩ ማኡና ሎአ እሳተገሞራ እአአ 10/27/2022

በማናቸውም ጊዜ ሊፈነዱ ይችላሉ ከሚባሉት እሳተ ጎመራዎች ትልቁ የሆነው የሐዋዩ ማኡና ሎአ እሳተገሞራ መፈንዳት መጀመሩ ተነገረ፡፡ እሳተ ጎመራው በአካባቢ ያሉ ነገሮችን ወደ አመድነት ሲቀይር አንዳንዶቹም በአካባቢው እንዲወዳድቁ ማድረጉ ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የጆኦሎጂካል ጥናት ፍንዳታው በትልቋ ደሴት ላይ መታየት የጀመረው ትናንት እሁድ ሌሊት መሆኑን አስታውቋል፡፡

እስተጎመራው ይደርሳል ተብሎ ከተገመተበት አካባቢ ያልወጣ ባለመሆኑ በአቅራቢያው የሚገኙ የማኅረሰብ አባላትን የማይጎዳ መሆኑንን ማዕከሉ አመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ማዕከሉ በማኡና ሎ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከእሳተ ጎመራው ላቫ ፍሰቶች እንዲጠነቀቁ መክሯል፡፡

በቅርቡ በአካባቢው ለደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የሆነው እአአ በ1984 ፍንዳታ ከደረሰው ወዲህ ሳይንቲስቶች ሁኔታውን በቅርበት ሲከታተሉት መቆየታቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG