በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአየር ንብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች


ከአየር ንብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:38 0:00

ከአየር ንብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

የመንግሥታቱ ድርጅት ባዘጋጀውና ግብፅ ውስጥ በተካሄደው 27ኛ የወገኖች የአየር ንብረት ጉባዔ ኢትዮጵያ ለደን ልማት የሚውል 50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘቷን ሃገሪቱን ወክለው በጉዔው ላይ የተሳተፉ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

“ከጉባዔው ትልቅ ውጤት ይዘን መጥተናል” ያሉት የኢትዮጵያ የደን ዘርፍ ቡድንን ወክለው የተሳተፉት ዶ/ር ይተብቱ ሞገስ ፤ ከአየር ንብረት ለውጥ ኢንቨስትመንት ፈንድ ላይ ገንዘቡ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ መወሰኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን ወክለው በጉባዔው ላይ የተገኙት ተደራዳሪዎች ቡድን አባል አቶ ገብሩ ጀምበሬ በበኩላቸው በዚህ ጉባኤ የኪሳራና የጉዳት ፈንድ ለማቋቋም ስምምነት ላይ መደረሱ ትልቅ ውጤት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የገንዘብ ቋቱ የአየር ብክለትን ለመቀነስ፣ አፍሪካን ጨምሮ እጅግ ተጋላጭ የሆኑ ማኅበረሰቦችን ለማገዝና እንደሚረዳ ባለሞያዎቹ ገልፀው፤ ያላደጉና ችግሩን ለመቋቋም የተቸገሩ ሃገሮች ለሚያጋጥማቸው ጉዳት ከበለፀጉት ሃገሮች ካሳ የመጠየቅ መብት እንደሚሰጣቸውም ጠቁመዋል፡፡

“የበለፀጉት ሃገሮች የኃይል አጠቃቀም ሥርዓታቸውን እንዲቀይሩ የሚቀርበውን ምክረ ሐሳብ ለመተግበር ቁርጠኞች አይመስሉም” ሲሉ አቶ ገብሩ አስተያየት ሰጥተዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG