በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ዓርብ ዕለት ከተደረገ የሥራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ በርካታ ወጣቶች መታሰራቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በእስር ላይ የሚገኙ የከተማው ወጣቶች ቁጥር ከ200 እንደሚልቅ አንድ አስተያየት ሰጭ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግሯል፡፡
በእስር ላይ የሚገኙና ታስረው የተለቀቁ ወጣቶች ድብደባን ጨምሮ የተለያዩ ኢሰብዓዊ ድርጊቶች እንደተፈጸመባቸውም አስተያየት ሰጪው አብራርተዋል፡፡
በዞኑ ካለው የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በፖሊስ እየተፈለጉ በመሆኑ ከአካባቢው የተሰወሩ ወጣቶች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡
በሚባለው ልክ መረጃ የለኝም ያለው የደቡብ ፖሊስ ሁኔታውን እንደሚያጣራ አስታውቋል፡፡
/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/