በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻድ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 10 ወታደሮች ሞቱ


በምዕራብ ቻድ ባለ ወታደራዊ ይዞታ ላይ ጂሃዲስቶች ዛሬ ማለዳ አድርሰውታል በተባለ ጥቃት 10 ወታደሮች መገደላቸውን የሃገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ቻድ ከኒጀር፣ ካሜሩን እና ናይጄሪያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር አካባቢ ነው ተብሏል። ቦታው ቦኮ ሃራም እና ኢስላሚክ ስቴት በምዕራብ አፍሪካ ግዛት በሚል የሚጠሩት እስላማዊ አክራሪዎች ጥቃት ሲያደርጉ የከርሙበት ቦታ መሆኑን የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘገባ አመልክቷል።

ሟቾቹ ወታደሮች ወደ ስፍራው ያቀኑት አንድ ስልታዊ ቦታ ላይ እግራቸውን ለመትከል የነበረ ቢሆንም “ቦኮ ሃራም ጥቃት አድርሰውባቸዋልል” ሲሉ የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ብራህ ማሃማት ተናግረዋል፡፡

የቻድ ባለሥልጣናት ጂሃዲስቶችን ሁሉ ቦኮ ሃራም እያሉ እንደሚጠሩ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷልክ።

በቻድ ሃይቅ አካባቢ ያለው ሁከት መነሻው በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ከ13 ዓመታት በፊት ቦኮ ሃራም ጥቃት ከፍቶ 40 ሺህ ሰዎች ከሞቱና 2 ሚሊዮን ሰዎች ከተፈናቀሉበት ግዜ ጀምሮ ነው።

በእአአ 2014 ቦኮ ሃራም በርካታ ደሴቶችን ተቆጣጥሮ እንደመደበቂያ ይጠቀም የነበረ ቢሆንም፣ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ግን ከቡድኑ ተገንጥሎ የወጣው ኢስላሚክ ስቴት በምዕራብ አፍሪካ ግዛት ደሴቶቹን በመቆጣጠር ላይ ይገኛል።

በከፊል በራሃማ የሆነችውን ቻድ ለሠላሳ ዓመት የገዙት ኢድሪስ ዴቢ ለ38 ዓመት ልጃቸው ሥልጣኑን ባለፈው ዓመት አውርሰዋል።

XS
SM
MD
LG