በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዙማ ተመልሰው የእስር ጊዜያቸውን እንዲጨርሱ የሃገሪቱ ይግባኝ ፍ/ቤት አዘዘ


ጄከብ ዙማ
ጄከብ ዙማ

በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ የይግባኝ ፍ/ቤት የቀድሞው የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ጄከብ ዙማ በእስር በነበሩበት ወቅት የሕክምና አመክሮ የወሰዱት ካለ አግባብ ነው በሚል ተመልሰው የእስር ጊዜያቸውን እንዲያጠናቅቁ ሲል ትዕዛዝ አስተላልፏል።

የ80 ዓመቱ ዙማ ፍርድ ቤቱን ደፍረዋል በሚል በሰኔ 2015 በ15 ወራት እስር ሲቀጡ ነፍስ የቀጠፈ ተቃውሞ መቀስቀሱ ይታወሳል።

ዙማ ሁለት ወር በእስር ከቆዩ በኋላ እስከአሁን ግልጽ ባልነበረ የህክምና አመክሮ ተለቀዋል ሲል የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቧል።

አመክሮው የተሰጠው በደቡብ አፍሪካ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሲሆን፣ የአስተዳደሩ የህክምና ኮሚቴ ግን ዙማ አስፈላጊውን መመዘኛ ስለማያሟሉ በውሳኔው ሳይስማማ ቀርቶ ነበር ተብሏል።

የሃገሪቱ ጠቅላይ የይግባኝ ፍ/ቤት ዛሬ እንዳለው ግን ዙማ የተለቀቁት በህገወጥ መንገድ በመሆኑ ወደ ዘብጥያ ተመልሰው የእስር ግዜያቸውን እንዲያጠናቅቁ ሲል ተዕዛዝ አስተላልፏል።

ዙማ በእስር የተቀጡት በእርሳቸው የሥልጣን ዘመን የተንሰራፋውን ሙስና በተመለክተ በሃገሪቱ ለተቋቋመው መርማሪ ቡድን ምሥክርነት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነበር።

ከሁለት አሥርት ዓመታት በፊት ተፈጽሟል በተባለ የመሣሪያ ሽያጭም ሌላ የሙስና ክስ አለባቸው።

XS
SM
MD
LG