በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካታር ስታዲዮሞች የአልኮል መጠጦች ተከለከሉ


የዘንድሮ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከሚካሄድባቸው የካታር ስቴዲዮሞች አንዱ
የዘንድሮ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከሚካሄድባቸው የካታር ስቴዲዮሞች አንዱ

በካታር በሚካሄደው የዘንድሮ የዓለም ዋንጫ እግር ኳስ ውድድር ላይ በስምንቱም ስቴዲዮሞች የአልኮል መጠጦች ሽያጭ ክልክል መሆኑን ፊፋ ትናንት ዓርብ ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል፡፡

ከአልኮል ነጻ የሆኑ የቢራ መጠጦች በስቴዲዮሙ ውስጥ እንደሚሸጡ ተገልጿል፡፡

ቢራዎችን መሸጥ የሚቻለው የግል መስተንግዶ በሚካሄድባቸው እንግዳ መቀበያ ስፍራዎች እንዲሁም ከጨዋታው በፊትና በኋላ በተከለሉ የዝግጅቱ አካባቢዎች እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በካታር እንደሚደረግ ከተነገረበት እኤአ ከ2010 ጀምሮ እስልምና እምነት ከፍተኛውን ሥፍራ በያዘባት ና ወግ አጥባቂ በሆነችው ካታር የአልኮል መጠጥ ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም የሚለው ሲያከራክር መቆየቱ ተነግሯል፡፡

እኤአ ከ1986 ጀምሮ ሚሊዮን ዶላሮችን እየከፈለ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድሮችን ስፖንሰር የሚያደርገው ቢራ ጠማቂው በድዋይዘር በትዊተር ገጹ ላይ ውሳኔውን አስመልክቶ የተናገረው አንዲት ቃል “ይሁና! ይህ የማይገባ ነገር ነው” ማለቱ ተዘግቧል፡፡

የትናንቱ የፊፋ ውሳኔ የመጣው ነገ ከሚጀመረው የዓለም ዋንጫ እግር ኳስ ውድድር ጨዋታ በፊት ነው፡፡

XS
SM
MD
LG