በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ከሺ ጂፒንግ ጋር ተነጋገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ከቻይናው መሪ ሺ ጂፒንግ ጋር በታይላንድ ባንኮክ በተካሄደው የእስያ ፓስፊክ ኢኮኖሚ ትብብር ፎረም ላይ (ፎቶ ዋይት ሀውስ ኖቬምበር 19 2022)
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ከቻይናው መሪ ሺ ጂፒንግ ጋር በታይላንድ ባንኮክ በተካሄደው የእስያ ፓስፊክ ኢኮኖሚ ትብብር ፎረም ላይ (ፎቶ ዋይት ሀውስ ኖቬምበር 19 2022)

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ ከቻይናው መሪ ሺ ጂፒንግ ጋር በባንኮክ በተካሄደው የእስያ ፓስፊክ ኢኮኖሚ ትብብር ፎረም ወደ ዝግ ስብሰባ ከመግባታቸው በፊት ለአንድ አፍታ ቆይታ አድርገው መነጋገራቸው ተነገረ፡፡

“ምክትል ፕሬዚዳንቷ፣ ባለፈው ሰኞ ህዳር 5 ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ከፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ ጋር ተገናኝተው በተነጋገሩበት ወቅት፣ በሁለቱ አገሮቻችን መካከል ያለውን ውድድር በኃላፊነት ለመምራት የግንኙት መስመሮቻችንን ክፍት ማድረግ ይኖርብናል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩትን ቁልፍ መልዕክት አስታውሰዋል ሲል” ዋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የምክትል ፕሬዚዳንቷ መልዕክት ቻይናን ሊያስከፋ ከሚችለው የፊሊፒንሷ ደሴት ፓላዋን የማክሰኞ ጉብኝታቸው ጋር ሊቃረን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ቻይና በደቡብ ቻይና ባህር በምትገኘዋ ፓላዋን ደሴት አካባቢ በዙሪያው ከሚገኙ የማሌዥያ፣ ፊሊፒንስ፣ ታይዋን እና ቬትናም አገሮች ጋር የይገባኛል ጥያቄ ያላት መሆኑ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG