ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ግጭት በዘላቂነት የማቆም ሥምምነቱን ተከትሎ ምግብ የጫኑ ከ80 በላይ ተሽከርካሪዎች በአራት ኮሪዶሮች ትግራይ ክልል መግባታቸውን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ከሥምምነቱ በኋላ ትግራይ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ተኩል ሰው እርዳታ ማግኘቱን መንግሥት ቢያስታውቅም ከህወሐት በኩል ግን የተሰማ ነገር የለም።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ መኪኖች ከኮምቦልቻ ተነስተው ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን ዛሬ አረጋግጧል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ።