በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ከቻይና ጋር “የጋራ ትብብር ያስፈልጋል” አሉ 


ፕረዘዳንት ጆ ባይደን ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂፒንግ ጋር በኢንዶኔዥያ ባሊ
ፕረዘዳንት ጆ ባይደን ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂፒንግ ጋር በኢንዶኔዥያ ባሊ

ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂፒንግ ጋር በኢንዶኔዥያው ባሊ ደሴት ነገ ማክሰኞ ከሚካሄደው ከቡድን 20 ጉባዔ በፊት ዛሬ ሰኞ አስቀድመው የተገናኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፣ በቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ መሃከል “የጋራ ትብብር ያስፈልጋል” ሲሉ አሳሰቡ፡፡

በሁለቱ አገሮቻቸው መካከል ያለው ግንኙነት በአስርት ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛው ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን የተመለከተ ሲሆን የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ ከባይደን ጋር “ግልጽና ጥልቅ የአስተያየት ልውውጥ ማድረግ እፈልጋለሁ” ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ከኢንዶኔዥያው ፕሬዚዳንት ጃኮ ዊዶዶ ጋር ጋር የተወያዩ ሲሆን በኤክሶን ሞቢል እና የኢንዶኔዥያ መንግሥት የኃይል ምንጭ ኩባንያ በሆነው ፔርታሚና መካከል ካርቦንን በማቆር (የካርቦን ልቀትን ሰብስቦ በመያዝ) ዙሪያ የተደረገውን የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ጨምሮ ኢንዶኔዥያ ውስጥ ተግባራዊ ይሆናሉ የተባሉ በርካታ ኢንቨስትመንቶችን ማስተዋወቃቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG