ፕሬዚዳንት ባይደን ኮፕ27 ተብሎ በሚጠራው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ግብጽ አምርተዋል። በአገር ውስጥና በሌሎች ሃገሮች የተከሰተውን የአየር ንብረት ቀውን ዩናይትድ ስቴትስ እንዴት እደታገለችው ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።
የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ተሟጋቾች ግን ባለፀጋ የሆኑ ሃገሮች የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለውን ጉዳት ለመጠገን እንዲውል ቃል የገቡትን 100 ቢሊዮን ዶላር እንዲሰጡ በመወትወት ላይ ናቸው።
የቪኦኤዋ አኒታ ፓወል የላከችውን አችር ዘግባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል፡፡