የማሊ የጦር ሠራዊት እና ጂሃዳዊ ቡድኖች ጅምላ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል፣ በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም አድርሰዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወነጀለ።
የመንግሥታቱ ድርጅት ይህን ያለው በሲቪሎች ላይ የተፈጸሙ ካሁን ቀደም በሰነድ ያልተመዘገቡ አድራጎቶችን በዘረዘረበት ሪፖርት መሆኑን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
በመንግሥታቱ ድርጅት የማሊ ተልዕኮ ሙኒስማ የቀረበው ሪፖርት እአአ ካለፈው ሀምሌ እስከ መስከረም በነበረው ግዜ 375 የመብት ጥሰት ድርጊቶች ተፈጽመዋል ያለ ሲሆን አንድ መቶ ስድሳ ሦስቱን በጂሃዳዊ ቡድኖች አንድ መቶ ስድሳ ሁለቱን ደግሞ በመንግሥቱ የጦር ሠራዊት የተፈጸሙ መሆናቸውን እንደሚያሳይ ዘገባው አመልክቷል።
የማሊ መንግሥት ውንጀላውን አስተባብሏል።