በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ አድማ ላይ ያለው ግብጻዊ የዲሞክራሲ ትግል አንቂ ሁኔታ


ፎቶ ፋይል፦ በግብጽ እስር ቤት በረሃብ አድማ ላይ ያለው አፍቃሪ ዲሞክራሲ አንቂ አላ አብደልፋታህ ካይሮ፣ ግብጽ 09/22/2014
ፎቶ ፋይል፦ በግብጽ እስር ቤት በረሃብ አድማ ላይ ያለው አፍቃሪ ዲሞክራሲ አንቂ አላ አብደልፋታህ ካይሮ፣ ግብጽ 09/22/2014

በግብጽ እስር ቤት በረሃብ አድማ ላይ ያለው አፍቃሪ ዲሞክራሲ አንቂ አላ አብደልፋታህ ቤተሰቦች የህክምና ዕርዳታ እንደተደረገለት በእስር ቤቱ ባለስልጣናት እንደተነገራቸው ገለጹ።

ለበርካታ ወራት የረሃብ አድማ ያደረገው አንቂው ባለፈው ሳምንት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔው ግብጽ ውስጥ ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ውሃም መጠጣት እንዳቆመ የተናገሩት ቤተሰቦቹ ምን ዓይነት ህክምና እንደተደረገለት በዝርዝር የተነገረን ነገር የለም ብለዋል።

በተመዱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ-27) የየእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ፣ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት

ኢማኑዌል ማክሮን እና የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሹልዝ ከግብጹ ፕሬዚደንት አብደልፋታህ ኤል ሲሲ ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች የዲሞክራሲ ትግል አንቂውን ስለአብደልፋታህን ጉዳይ እንዳነጋገሯቸው ተገልጿል።

የእስር ቤቱ ባለሥልጣናት የአብዱልፋታህ ጠበቆች ገብተው እንዳያነጋገሩት ከልክለዋቸዋል።

የሰብዐዊ መብት ድርጅቱ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሃፊ አግነስ ካላማርድ "በግብጽ እስር ቤቶች ለእስረኞች የሚሰጠው ህክምና እጅግ አስከፊ በመሆኑ ከመንግሥት ነጻ የህክምና ዕርዳታ ሊደረግለት ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG