ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ እየተካሄደ ከሚገኘው የአጋማሽ ዘመን የምክር ቤት እና የአካባቢ ምርጫ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር "የአሜሪካ ዲሞክራሲ ጥቃት እየደረሰበት ነው" ብለው ነበር።
ለዚህም ከርሳቸው በፊት ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶናልድ ትረምፕ የምርጫ ውጤቱን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን እንደምክንያትነት ጠቅሰዋል።
በአሜሪካ ምክር ቤት ላይ የደረሰውን የጥር 6 ጥቃት እና ከሳምንታት በፊት በም/ቤቱ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ባለቤት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በመጥቀስም የፖለቲካ ሁከት እየጨምረ መሄዱን አመልክተዋል።
ሆኖም አንዳንድ ተንታኞች በአሜሪካ የዲሞክራሲ ማሽቆልቆል የጀመረው ከትረምፕ በፊትም እንደሆነ በመግለፅ ይከራከራሉ። ለመሆኑ የአሜሪካ ዲሞክራሲ የተደቀኑበት ፈተናዎች ምንድን ናቸው?
በሞርጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑትን ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ ማብራሪያ ሰጥተውናል።
/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/