በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤቱን ማንኛው ፓርቲ እንደሚቆጣጠር የሚወስነው የነገው ምርጫ


የምርጫ ሰራተኛ በኒውዮርክ፣ እአአ 11/72022
የምርጫ ሰራተኛ በኒውዮርክ፣ እአአ 11/72022

ዲሞክራቶች አብላጫ መቀመጫ እንደያዙ ይዘልቁ እንደሆን ወይም ሪፐብሊካኖች የተወካዮች ምክር ቤቱንም የህግ መወሰኛውንም ይቆጣጠሩ እንደሆን የሚለየው የዩናይትድ ስቴትስ የአጋማሽ ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣን ዘመን ምርጫ ነገ ማክሰኞ ይጠናቀቃል።

አንዳንድ ሪፐብሊካን ተፎካካሪዎች ምርጫው ተዓማኒ አይሆንም የሚል ነቀፌታ እያሰሙ ባለበት የፓርቲ ወገንተኛ ያልሆኑ ቡድኖች ሂደቱን በአንክሮ በመከታተል ላይ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት ዲሞክራቶች በኮንግሪሱ ጠባብ አብላጫ መቀመጫ አላቸው። የእስካሁን ታሪክ በዚህ ምርጫ ለሚሆነው በጠቋሚነት ከተወሰደ ግን የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዲሞክራቲክ ፓርቲ በተወካዮች ምክር ቤት ብዛት ያላቸው መቀመጫዎች በሴኔቱ ደግሞ ጥቂት መቀመጫዎችን በሪፐብሊካኖች ሊነጠቅ ይችላል።

ዲሞክራቶች የዋጋ ንረቱ አሜሪካውያንን እየጎዳ ቢሆንም የሴቶችን ጽንስ የማስወረድ መብት በቀለበሰው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ምክንያት መራጮች ወጥተው ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ያመለክታሉ።

አንዳንዶቹ ሪፐብሊካን ዕጩ ተፎካካሪዎች በበኩላቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን ያለፈው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሰርቋል ውንጀላ የሙጥኝ ብለው የምርጫውን ተዓማኒነት ጉዳይ ዋና የዘመቻ ቅስቀሳቸው አጀንዳ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG