በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ የውጊያ ጄቶቿን በደቡብ ኮሪያ ድንበር አቅራቢያ አበረረች


FILE - In this image taken from video, South Korean Air Force's F15K fighter jet takes off Oct. 4, 2022, in an undisclosed location in South Korea.
FILE - In this image taken from video, South Korean Air Force's F15K fighter jet takes off Oct. 4, 2022, in an undisclosed location in South Korea.

ደቡብ ኮሪያ 180 የሚሆኑ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ በረራዎች በድንበር አቅራቢያ መደረጋቸውን ከተረዳች በኋላ የውጊያ ጄቶቿን አንቀሳቅሳለች።

የደቡብ ኮሪያ ጥምር ኃይል ዕዝ በሰጠው መግለጫ በርካታ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ በረራዎች ድንበር ዘልቀው ግብተውም ነበር ብሏል።

በምላሹ ደቡብ ኮሪያ 80 የሚሆኑ የጦር ጄቶቿን አንቀሳቅሳለች።

ወደ 240 የሚሆኑ የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ የጦር አውሮፕላኖች ከፍተኛ ወታደራዊ ከፍተኛ ልምምዳቸውን ቀጥለዋል ተብሏል። ልምምዱ እስከ ነገ እንደሚቀጥል ታውቋል። ይህም በእቅድ ከተያዘው አንድ ቀን የጨመረ ሲሆን፣ ምክንያቱ፣ ሰሜን ኮሪያ ትንኮሳዋን በመቀጠሏ ነው ተብሏል።

ሰሜን ኮሪያ ከረቡዕ ወዲህ ብቻ 30 ሚሳዬሎችን አስወንጭፋለች፣ አንዳንዶቹ ተኩሶች በደቡብ ኮሪያና በጃፓን የአስቸኳይ ግዜ ማስጠንቀቂያ እንዲወጣና ሰዎች ባሉበት እንዲጠለሉ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ አስገድደዋል።

ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካና በደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደርቃዊ ልምምድ ምክንያት ብስጭት ላይ ነች። ልምምዱ በተጠናከረ እንዲቀጥል የተደረገው ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ የመሣርያ ሙከራዋንና ሌሎች ዛቻዋን በምቀጠል ላይ በመሆኗ ነው ተብሏል።

XS
SM
MD
LG