በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት የዋጋ ግሽበትን የሚቆጣጠር ቦርድ እንዲያቋቁም ተጠየቀ


መንግሥት የዋጋ ግሽበትን የሚቆጣጠር ቦርድ እንዲያቋቁም ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:36 0:00

መንግሥት የዋጋ ግሽበትን የሚቆጣጠር ቦርድ እንዲያቋቁም ተጠየቀ

የኢትዮጵያ መንግሥት በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የዋጋ ግሽበት የሚቆጣጠርና የሚያረጋጋ ቦርድ እንዲያቋቁም የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ጠየቀ፡፡

ማኅበሩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እና የዋጋ ግሽበትን የሚዳስስ ጥናታዊ መፅሐፍ ያስመረቀ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበቱ በመስከረም ወር ላይ 32.5 በመቶ መድረሱን አመልክቷል፡፡

መንግስት ችግሩን ለመፍታት ባለፉት ሁለት አመታት አስር የፖሊሲ እርምጃዎችን ቢወስድም፣ ግሽበቱ ግን በተፈለገው ደረጃ ሊረጋጋ እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር እየጨመረ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለማረጋጋት መንግሥት በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ መውሰድ አለበት ያላቸውን የመፍትሔ ሀሳቦችን አስቀምጧል፡፡

ከመፍትሔዎቹ አንዱም የዋጋ ግሽበትን የሚያረጋጋ ቦርድ መቋቋም አለበት የሚል ነው፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG