የምርጫ አስፈፃሚ ሰራተኞች በመምረጫ ሥፍራዎች ከፍተኛ የስሜት መለዋወጥ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል መገመታቸው እና በቅርቡ በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፔሎሲ መኖሪያ ቤት የተፈፀመው ጥቃት ለዚህ ማሳያዎች ናቸው።
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ሌሎች ታላላቅ የፖለቲካ ሰዎች የፔሎሲን ባለቤት፣ ፖልን ክፉኛ ያቆሰለውን ጥቃት በማውገዝ ህዳር ስምንት የሚካሄደው ምርጫ መቃረቡን ተከትሎ ሊቀሰቀስ የሚችል የፖለቲካ ሁከት እንዲቆም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።