በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ሩሲያ ከቅርብ ጊዜዎቹ የሚሳዬል ጥቃቶች በኋላ እንድትገለል ጠየቀች


የነፍስ አድን ሠራተኞች በሩሲያ የሚሳየል ጥቃት ከፈራረሰው ህንፃ የተገኘውን አስከሬን እያጓጓዙ፤ በማይኮላይቭ፣ ዩክሬን
የነፍስ አድን ሠራተኞች በሩሲያ የሚሳየል ጥቃት ከፈራረሰው ህንፃ የተገኘውን አስከሬን እያጓጓዙ፤ በማይኮላይቭ፣ ዩክሬን

በበርካታ የዩክሬን ከተሞች መሰረተ ልማትን ኢላማ በማድረግ ጥቃት የሰነዘረቸው ሩሲያን ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲያገልሏት የዩክሬን ባለሥልጣናት ጠየቁ፡፡

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኦሌግ ኒኮሌንኮ ዛሬ ማስከኞ በሰጡት መግለጫ ሩሲያ ከቡድን 20 አባል አገራት እንድትገለል እና የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዚህ ወር በኤንዶኔዥያ የቡድን 20 ጉባኤ ላይ እንዲካፈሉ የተላከላቸው ግብዣ እንዲሰረዝ ጠይቃለች፡፡

ኒኮሌንኮ ባወጡት የትዊት መልዕክት “ፑቲን በዩክሬን የህዝብና የኃይል ምንጭ በሆኑ የአገልግሎት ሰጭ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሳዬል ጥቃት እንዲካሄድ ማዘዛቸውን በይፋ አምነዋል” ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አያይዘውም ፕቱን “በደም ከጎደፈው እጃቸው ጋር ከዓለም መሪዎች ጋር በአንድ ጠረጴዛ ላይ እንዲቀመጡ ሊፈቀድላቸው አይገባም” በማለት ተናግረዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንትናንት ሰኞ በሰጡት መግለጫ ጥቃቶቹ የተሰነዘሩት ኪየቭ በጥቁር ባህር ላይ በነበሩ የሩሲያ መርከቦች ላያ አድርሳዋለች ላሉት ጥቃት የተሰጠ ምላሽ ነው ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG