በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌና ቦሰት ወረዳዎች መንግሥት ሸኔ በሚለው እና ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን ተፈጸመ ባሉት ጦቃት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው እየተመለሱ ነው ሲል የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።
በመስከረም ወር ተፈጸመ በተባለው ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ክልል መሰደዳቸውን በሃዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ እና በካምባታ ዞን የተጠለሉ ተጎጂዎች ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ገልፀዋል።
ተፈናቂዎቹ አክለውም የመተሃራ እና አካባቢው ጥቃት የፈጸመው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና የኢትዮጵያ ፓርላማ ግን ሸኔ በሚል በአሸባሪነት የፈረጀው ቡድን ነው ይላሉ። በጥቃቶቹ 14 ሰዎች መገደላቸውንም ተናግረዋል።
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]