በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"እህልን በመሳሪያነት እየተጠቀመች ነው " ሲሉ ብሊንከን ሩሲያን ከሰሱ


ብሊንከን የሩሲያ መንግስት ዳግም ወደ ትግበራው እንዲመለስ እና በመላ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ተጠቃሚነታቸውን እንዲቀጥሉ እንዲሰራ አሳስበዋል ።
ብሊንከን የሩሲያ መንግስት ዳግም ወደ ትግበራው እንዲመለስ እና በመላ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ተጠቃሚነታቸውን እንዲቀጥሉ እንዲሰራ አሳስበዋል ።

ሞስኮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አደራዳሪነት ስምምነት ከተደረሰበት ከዩክሬን ወደ ሌሎች ሀገራት እህል የመላኩን ትግበራ መቋረጧ ተሰምቷል። ይህ ስምምነት የዓለምን የምግብ ቀውስ እና ዋጋ ለመቀነስ የሚያስችል ከ9 ሚሊየን ቶን በላይ እህል ከዩክሬን ወደ ሌሎች ሀገራት እንዲላክ ይፈቅድ ነበር ።

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ፣ሩሲያ በተቆጣጠረችው በክሪሚያ ዳርቻ ጥቁር ባህር ላይ በነበሩ መርከቦች ላይ ዩክሬን የድሮን ጥቃት መክፈቷን ለአሁኑ ውሳኔ በምክንያትነት አቅርቧል ። ሩሲያ ጥቃቱ የተፈጸመው ቅዳሜ ዕለት መሆኑን ብትገልጽም ፣ ዩክሬን ግን ውንጀላውን አስተባብላለች ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንተኒ ብሊንከን ባወጡት መግለጫ ፣ ሩሲያ ስምምነቱን በማቋረጥ ቀድሞውኑም እራሷ በጀመረችው ጦርነት ውስጥ ምግብን በመሳሪነት እየተጠቀመች መሆኑን አስታውቀዋል። በዚህም በቀጥታ የሚጎዱት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ እንደሆነ፣ አጣዳፊውን የሰብዓዊ ድጋፍ ቀውስ እና የምግብ ዋስትና እንደሚያባብሰው ገልጸዋል ።ብሊንከን የሩሲያ መንግስት ዳግም ወደ ትግበራው እንዲመለስ እና በመላ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ተጠቃሚነታቸውን እንዲቀጥሉ እንዲሰራ አሳስበዋል ።

የሩሲያ ውሳኔ የተሰማው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አቶኒዩ ጉቴሬዝ ሩሲያ እና ዩክሬን እህል ተኮሩን ስምምነት እንዲያድሱ ባሳሰቡ ማግስት ነው።

XS
SM
MD
LG