በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኳታር ከዐለም ዋንጫ በፊት በዋና ከተማዋ የሚሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ከከተማይቱ አባረረች


የቀን ሰራተኞች በኳታር 2022
የቀን ሰራተኞች በኳታር 2022

ኳታር በዐለም ዋንጫው ወቅት ሃገር ጎብኚ የእግር ኳስ ደጋፊዎች በሚያርፉበት በዋና ከተማዋ ዶሃ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ሃገር ዜግነት ያላቸው ሰራተኞች ከሚኖሩበት የመኖሪያ ህንጻ ማስለቀቋን ሮይተርስ ዘገበ።

ነዋሪዎቹ በተለይም ደግሞ እስያውያን እና አፍሪካዊያን ሰራተኞች ይኖሩባቸው የነበሩ ከ12 በላይ የሚሆኑ የመኖሪያ ህንጻዎች በባለስልጣናት አማካኝነት መና እንዲቀሩ መደረጋቸውን እና

መዘጋታቸውን ነዋሪዎቹ አስታውቀው በዚህም የተነሳ ከጎዳና ለማደር መገደዳቸውን እና መጠለያ በማፈላለግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አል መንሱራ በተሰኘ የዶሃ አካባቢ ካለ አንድ ህንጻ ላይ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የኳታር ባለስልጣንት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ 1200 ሰዎች ወደ ሚኖርበት ህንጻ በመምጣት በ2 ሰዓታት እድሜ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እንደነገሯቸው አስታውቀዋል።

ይህ የኳታር እርምጃ የዐለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከመጀመሩ ከአራት ሳምንታት ባነሰ ጊዜ የተደረገ ሲሆን፤ ይህም ኳታር የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሰራተኞች ላይ የምታራምደው ጥብቅ የማኅበራዊ ህግ፣ ገደብ እና አያያዝ በዐለም ዙሪያ ለብርቱ ትችት እና ግምገማ አጋልጧታል።

ሮይተርስ ያነጋገራቸው በጎዳና ላይ የሚያድሩ ሰዎች በኳታር መንግስት ሊከተልባቸው የሚችለውን ቅጣት በመስጋት ስማቸውንም ሆነ ማንነታቸውን መግለጽ እንደማይሹ ዘግቧል።

በአንጻሩ የኳታር ባለስልጣናት የአሁኑ ውሳኔ ከዐለም እግር ዋንጫ ጋር የሚያያዝ ሳይሆን “የዶሃን መደሮችን መልሶ ለማስተካከል የተያዘ የረዥም ጊዜ እቅድ አካል ነው”ሲሉ “ሁሉም ግለሰቦች አስቀድሞ ተገቢ የሆነ ማሳሰቢያ የደረሳቸው ሲሆን በአሁን ሰዓትም ተገቢ የሆነው መኖሪያ ተሰጥቷቸዋል” ብለዋል።

ኳታር ሦስት ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎችን ቀጥራ የምታሰራ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 85 በመቶ ያህሉ የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው። በአሁን

ሰዓት መኖያቸውን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉት አብዛኞቹ ሰራተኞችም የራሳቸውን መኖሪያ እና ቀለብ በራሳቸው የሚሸፍኑ የነበሩ ሹፌሮች እና ለተለያዩ ኩባኒያዎች በኮንትራት ይሰሩ የነበሩ የቀን ሰራተኞች ናቸው።

XS
SM
MD
LG