በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ ውስጥ ሁለት ፈንጂ የተጠመደባቸው ተሽከርካሪዎች ባደረሱት ጥቃት በርካቶች ህይወታቸውን አጡ


በሶማሊያ ትምህርት ሚኒስቴር የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት
በሶማሊያ ትምህርት ሚኒስቴር የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሚገኘው ዞቤ ከተሰኘ መስቀለኛ መንገድ አቅራቢያ ከሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር ላይ በተነጣጠረ አጥፍቶ ጠፊዎች በሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ ያጠመዱት ቦምብ ፈንድቶ ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክኒያት መሆኑን እማኞች እና የጸጥታ ባለስልጣናት ገለጹ።

የመጀመሪያው የቦንብ ጥቃት የተፈጸመው ከትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ጊቢ መግቢያ ከሚገኝ የፍተሻ ሥፍራ ሲሆን፤ ሁለተኛው ፍንዳታ ደግሞ ተጎጂዎችን ለመርዳት ሲሯሯጡ የነበሩ ግለሰቦች እና የአምቡላንስ ሰራተኞች ከመጡ በኋላ መፈጸሙን ስማችቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

“እጅግ ብዙ ሰዎች በጉዳቱ ህይወታቸው አልፏል” ያሉት የሶማሊያ የፖሊስ ቃል አቀባይ ሳዲቅ ዶዲሼ፤ ሆኖም እስካሁን በሁለቱም ጥቃቶች የተገደሉት ሰዎች ትክክለኛ አሃዝ እንደሌላቸው እና ምርመራው ሲጠናቀቅ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በአንጻሩ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች በአደጋው የሞቱት ሰዎች ቁጥር በጥቂቱ 20 እንደሚደርስ አስታውቀዋል።

ለዛሬው ጥቃትም እስካሁን ድረስ ሃላፊነቱን የወሰደ ቡድን ባይኖርም፣ በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው እስላማዊ ቡድን አል ሸባብ በተደጋጋሚ ይህን መሰል ጥቃቶች በሃገሪቱ መዲና ሞቃዲሹ እንደሚፈጽም ይታወቃል።

የዛሬው ጥቃትም የተፈጸመው የሃገሪቱ ፕሬዘዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና የፌደራል ክልል አባል መሪዎች ጽንፈኛ ርዕዮተ አለምን ለመዋጋት እና ለማጥፋት ለአምስት ቀናት የተካሄደው ብሔራዊ ኮንፈረን ላይ ከተገኙ ሰዓታት በኋላ ነው

XS
SM
MD
LG