በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ሁለት ባልስቲክ ሚሳዬል ማስወንጨፏን ደቡብ ኮሪያ አስታወቀች


የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራን የሚያሳይ የዜና ስርጭት
የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራን የሚያሳይ የዜና ስርጭት

ሰሜን ኮሪያ ሁለት ባልስቲክ ሚሳዬል ዛሬ ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ ሰራዊት አስታውቋል፤ በዚህም ከአሜሪካና አጋሮቿ ጋር ያለውን ውጥረት አባብሳለች ተብሏል።

ሰሜን ኮሪያ ሁለት የአጭር ርቀት ባሊስቲክ ሚሳዬሎችን በምስራቅ ድንበሯ በኩል ወደ ባህር መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጣምራ ጦር አስታውቋል።ሚሳዬሎቹ ደቡብ ኮሪያን ከሚያገናኘው ግዛት እንደተተኮሱም ታውቋል።

በአካባቢው ያለው የአሜሪካ ኢንዶ-ፓሲፊክ ዕዝ፣ ተኩሱ በዜጎቿ፣ በግዛቷም ሆነ በሸሪኮቿ ላይ የሚያስከትለው አደጋ ባይኖርም፣ የሰሜን ኮሪያን የመሣሪያ ፕሮግራም አፍራሽ ተጽዕኖን የሚያመላክት ነው ሲል አስታውቋል።

ሰሜን ኮሪያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በቁጥር እስከአሁን ከፍተኛ የሆነውንና 46 ሚሳዬሎችን አስወንጨፋለች። የባልስቲክ ሚሳዬል እንቅስቃሴ እንዳታደርግ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤት ውሳኔ የታገደችው ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት 46 ግዜ ውሳኔውን ጥሳለች ማለት ነው።

ፒዮንግያንግ በቅርቡ 7ኛውን የኑክሌር ሙከራ እንደምታደርግም በስፋት እየተጠበቀ ነው። ይህም ከ5 ዓመታት ወዲህ የመጀመሪያው ሊሆን ነው።

ሙከራው ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ፕሮግራሟን በከፍተኛ ደረጃ እያከናወነች መሆኑንና ይህም እጅግ አስጊ ጉዳይ መሆኑን የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ድርጅት ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ ተናግረዋል።

“ተስፋችን የኑክሌር ሙከራው እንዳይደረግ ነው፤ ነገሮች የሚያሳዩት ግን ተቃራኒው ነው” ብለዋል ኃላፊው።

ከአራት ቀናት በፊት አንድ የስሜን ኮሪያ የንግድ መርከብ የባህር ድንበንሩ አልፎ ከገባ በኋላ፣ ሁለቱ ኮሪያዎች የማስጠንቀቂያ ተኩስ ተለዋውጠዋል።

አሜሪካና ደቡብ ኮሪያብ በአካባቢው የሚያደርጉትን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እንደቀጠሉ ነው።

XS
SM
MD
LG