በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኡጋንዳ ስድስት ህጻናት በኢቦላ ተያዙ


የሙቤንዴ ክልላዊ ሪፈራል ሆስፒታል ዶክተሮች የኢቦላ ክፍል ዩጋንዳ
የሙቤንዴ ክልላዊ ሪፈራል ሆስፒታል ዶክተሮች የኢቦላ ክፍል ዩጋንዳ

በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ በሚገኙ ሦስት የተለያዩ ት/ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ስድስት ህጻናት በኢቦላ መያዛቸው ተነግሯል። አንደኛው ሕጻን በተውሳኩ ህይወቱን ተነጥቋል።

ስድስቱ ህጻናት በአንድ መንደር እንደሚኖሩና፣ በበሽታው ምክንያት ከሞተ እንድ ሰው እንደተላለፈባቸው የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ጄን ሩት አሰንግ አስታውቀዋል።

ከልጆቹ ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው የሚችል 170 ሰዎች መለየታቸውንና ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል። በሽታው የተሰፋፋው የታመሙ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መሄድ በመተዋቸው ነው ብለዋል።

ባለፈው መስከረም አንድ የ24 ዓመት ግለሰብ በምርመራ ኢቦላ እንደተገኘበት ከታወቀ በኋላ፣ የኡጋንዳ መንግሥት በሽታው መከሰቱን አውጇል።

እስከ አሁን 31 ሰዎች በኢቦላ በሽታ ምክንያት ሲሞቱ፣ 109 ደግሞ ተይዘዋል።

XS
SM
MD
LG