በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢላን መስክ ተጠያቂነት ያለበት ትዊተር እንዲኖር ይሻሉ


ኢላን መስክ
ኢላን መስክ

ኢላን መስክ “ሰብዓዊነትን ለመደገፍ” ሲሉ ትዊተርን እንደሚገዙና፣ ተጠያቂነት የሌለበት “ሁሉም በነጻ የሚፈነጭበት ቦታ” እንዲሆን እንደማይፈልጉ በዛው በትዊተር ዛሬ አስታውቀዋል።

መስክ በትዊተር ማስታወቂያ ለሚያስነግሩና ለሚያስተላልፉ የማስታወቂያ ድርጅቶች የላኩት መልዕክት የመጣው፣ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን በመግዛት የግላቸው ሊያደርጉ አንድ ቀን በቀረበት በዛሬው ዕለት ነው።

በሌላኛው የትዊተር መልዕክታቸው መስክ፣ የባኞ ቤት የእጅ መታጠቢያ ገንዳ ይዘው ሲገቡ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቅቀው “ወደ ትዊተር ዋና መሥሪያ ቤት እየገባሁ ነው። ይግባችሁ ተረዱት!” ብለዋል።

የእጅ መታጠቢያው ወይም በእንግሊዝኛ ሲንክ የሚባለውን ተሸክመው የገቡትም “Let that sink in” ተረዱት፣ ይግባችሁ፣ ለማለት ነው ተብሎ ተገምቷል።

“ትዊተርን የምገዛው የወደፊቱ ሥልጣኔ፣ ወደ ሁከት ሳይገባ በጤናማ መንገድ፣ የተለያዩ እምነቶች የሚስተናገዱበት አደባባይ ስለሚያስፈልገው ነው “ ብለዋል ቢሊየነሩ መስክ።

XS
SM
MD
LG