በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት ሳቢያ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በጥቂት ሳምንታት ዕድሜ ሊፈተኑ ነው


በግጭት ሳቢያ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በጥቂት ሳምንታት ዕድሜ ሊፈተኑ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:40 0:00

በግጭት ሳቢያ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በጥቂት ሳምንታት ዕድሜ ሊፈተኑ ነው

በኢትዮጵያ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ድረስ የተሰጠውን የ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በግጭት ምክንያት ያልወሰዱ 56 ሺህ ተማሪዎች በአንድ ወር ውስጥ ሌላ ፈተና እንደሚወስዱ ተገለፀ፡፡ የብሔራዊ ፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክተው መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ዋናውን ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎችም በአንድ ወር ውስጥ የሚሰጠውን ሁለተኛውን ፈተና እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡

ከአራት የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን ጥለው የወጡት 12 ሺህ ተማሪዎች ግን ዳግም እንደማይፈተኑ፣ ሆኖም በግል የመፈተን መብታቸው እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የፈተናውን አፈፃፀም በተመለከተ ባደረጉት ገለፃ፣ ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት የተለያዩ ችግሮችና አደጋዎች ማጋጠማቸውን ተናግረው፣ የፈተና ስርቆት ግን አላጋጠመም ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG