በጋምቤላ ክልል በጎርፍ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥእንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታውቋል ።
እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍም ተመጣጣኝ አይደለም ብሏል።
ካለፈው አመት ነሐሴ ጀምሮ እስከአሁኑ ጥቅምት ወር የጣለው ዝናብባስከተለው ጎርፍ በጋምቤላ ክልል ከሚገኙ 12 ወረዳዎች ውስጥ ከ185 ሺ በላይየሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውንም ጽ/ቤቱ ትናንት ባወጣው ሪፖርትአመልክቷል።
የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት በበኩሉ ተፈናቃዮችወደየአካባቢያቸው እየተመለሱ ነው ብሏል።
የተመለሱትን ሰዎች ቁጥር ግን አልጠቀሰም።