በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሪሺ ሱናክ አዲሱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ነው


ፎቶ ፋይል፡ የእንግሊዝ የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ
ፎቶ ፋይል፡ የእንግሊዝ የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ

የእንግሊዝ የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ፣ ለእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያበቃቸውን ውድድር ማሸነፋቸው ተነገረ፡፡

የ42 ዓመቱ ሱናክ፣ ከ200 ዓመታት በላይ በዘለቀው የብሪታኒያ ታሪክ በእድሜ ትንሹ፣ የመጀመሪያው ነጭ ያልሆኑ የሂንዱ እምነት ተከታይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑም ተመልክቷል፡፡

በእንግሊዝ የመገናኛ ብዙሃን “ዲሺ ሪሺ” በሚል የቁልምጫ ስም የሚጠሩት ሱናክ ያላቸው የወጣትነት ቁመና ቄንጠኛው አለባበሳቸውና በራስ የመተማመን ስሜት ያላቸው ወጣቱ የፖለቲካ ሰው መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ሪሺ ሱናክ፣ የሚቀጥለው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን ይችላሉ የሚለውን ዜና የለንደን ነዋሪዎች በደስታ መቀበላቸው ቀደም ባለው ዘገባ ተመልክቷል፡፡

ባላፈው ሀምሌ በነ ምግባር ጉድለት ከሥልጣናቸው የተወገዱት ቦሪስ ጆንሰን፣ ባላፈው ሳምንት ራሳቸውን ከሥልጣን ያገለሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ በመተካት ለገዥው የወግ አጥባቂው መሪነት እንደሚወዳደሩ በስፋት ተጠብቆ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ጆንሰን ለእረፍት ከነበሩበት የካሪቢያን ደሴት ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ባላፈው ቅዳሜና እሁድ ከህግ አውጭዎቹ የምክር ቤት አባላት ደጋፊዎቻቸው ድጋፍ ለማሰባሰብ መሞከራቸው ተመልክቷል፡፡

ትናንት እሁድ ለእጩነት የሚያበቃቸውን ከ100 በላይ የምርክ ቤት አባላት ስሞችን ማሰባሰብ መቻላቸውን ገልጸው እንደነበርም ማስታወቃቸው ተገልጿል፡

ይሁን እንጂ ሱናክ ከጆንሰንና ከቀድሞው የካቢኒ ሚኒስትር ፔኒ ሞርዳውንት ከፍ ባለ መጠን ከ100 በላይ የወግ አጥባቂው ፓርቲ የፓርላማ አባላት ያሉበትን ጠንካራ የህዝብ ድጋፍ ማግኘት መቻላቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG